በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ መሪዎች መታሠር እና ውዝግቡ


የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት የታወቁ የፖለቲካ ተቃዋሚ መሪዎችን ይዞ ማሠሩን አስታውቋል።

አንደኛው የኦሮሞ ሕዝብ ኰንግሬስ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦልባና ሌሊሳ ሲሆኑ ሁለተኛው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበርና የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኰሚቴ አባል አቶ በቀለ ገርባ ናቸው።

አቶ በቀለ ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ የታሠሩት ሕገወጥ ከተባለው ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ቀርቦባቸው መሆኑን የመንግሥቱ ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ስለ አቶ ኦልባና ግን የተገለፀ ነገር የለም።

ሰሎሞን ክፍሌ በዩናይትድ ስቴትስ የሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኙትን የፓርቲውን መሪ ዶክተር መረራ ጉዲናን «የዲሞክራሲ በተግባር» ፕሮግራሙ እንግዳ አድርጓቸዋል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG