በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት የተቃዋሚ መሪዎች ታሠሩ፤ አንዱ በሽብር ፈጠራ ተጠርጥረዋል

የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት ታዋቂ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ይዞ አሥሯል፡፡ የአንደኛው ክስ 'በሽብር ፈጠራ ነው' ተብሏል፡፡ ይህንን የመንግሥት እርምጃ በፖለቲካ ምክንያት የተነሣሣ ነው ሲሉ ተቃዋሚ መሪዎች አውግዘውታል፡፡

ነባር የተቃዋሚ መሪ ናቸው የሚባሉት በቀለ ገርባ የተያዙት 'በኢትዮጵያ መንግሥት በሽብር ፈጠራ ቡድንነት ተፈርጆ ከታገደው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ግንኙነት አላቸው' በሚል መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥታ ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር የሆኑት በቀለ ገርባ በኢትዮጵያ ትልቁ ነው የሚባለው ተቃዋሚ ጥምረት፣ የመድረክ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባና የኦሮሞ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀ መንበር ናቸው፡፡

ሌላው የኦሮሞ ተቃዋሚ መሪ የሆኑት የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረሱ ኦልባና ሌሊሣም እንዲሁ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የኦልባና ጉዳይ ከሽብር ፈጠራ ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ለጊዜው አልተገለፀም፡፡

ሁለቱም ሰዎች ለየፓርቲያቸው ከውጭ አካላት ጋር ግንኙነቶችን ያደርጉ እንደነበር የወቅቱ የመድረክና የኦሮሞ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር በቀለ ገርባ ገልፀዋል፡፡

በዚያ የፓርቲ ኃላፊነቶቻቸውም በደቡብ ኢትዮጵያ በርቀት አካባቢዎች ውስጥ ስላለው የድርቅና የምግብ እጥረት ሁኔታ መረጃ እንደሚሰጡ ዶ/ር ሞጋ ጠቁመው እነዚያ መረጃዎች የሚይዟቸው ጭብጦች አንዳንድ ጊዜ መንግሥት ከሚለው ጋር እንደሚጋጩ አመልክተዋል፡፡

በተለይ በቀለ ገርባ የኢትዮጵያ መንግሥት በቢልዮኖች ዶላር የሚቆጠር የእርዳታ ገንዘብ 'ለፖለቲካ ጭቆና ያውላል' በሚል ቢቢሲ ላወጣው ዘገባ 'መረጃ ሰጥታችኋል' ተብለው ስለታሠሩ ሰዎች ይናገሩ እንደነበር ዶ/ር ሞጋ ጠቁመዋል፡፡

የቢቢሲ ዘገባ ኃላፊነት የጎደለው ነው በሚል የኢትዮጵያ መንግሥት በብርቱ ተቃውሞታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዌብ ሣይት ላይ የወጣ መግለጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው ቡድን ቀደም ሲልም ተመሣሣይ ውንጀላዎችን ያሰሙ እንደነበርና ውንጀላዎቹ መሠረተ ቢስ ሆነው መገኘታቸውን ይናገራል፡፡

በቢቢሲው ዘገባ ውስጥ ከተነሡ ሰዎች መካከል ነባሩ የተቃዋሚ መሪ በየነ ጴጥሮስ የሚገኙበት ሲሆን ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ በሰጡት መግለጫ እርዳታ አግባብነት ለሌለው አድራጎት ማራመጃ ይውላል የሚለውን ክስ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

የበቀለ ገርባና የኦላና ሌሊሣም መታሠር 'አስደንጋጭ መረጃዎችን ለመገናኛ ብዙኃን የሚሰጡ ሰዎችን ሊያሸማቅቅ የሚችል የተለየ ሃሣብና አመለካከት ያላቸውን ሰዎች የማሣደድ ዘመቻ አካል ነው' ብለውታል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፡፡

የአሁኖቹ እሥሮች የተፈፀሙት መንግሥትን በብርቱ የሚተቹ ሁለት ጋዜጠኞች በሽብር ፈጠራ አድራጎት በተከሰሱበት ወቅት መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ክሦቹና እሥራቱ 'ተቃውሞን ለማፈን ሽብር ፈጠራን እንደሰበብ በማስቀደም የተፈፀሙ ናቸው' ሲሉ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ቡድኖች ሥጋታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

አቃቢያነ ሕጉ ግን ጋዜጠኞቹ በኤሌክትሪክና በስልክ መሥመሮች ላይ ተንኮል ሲሠሩ እንደነበር እየተናገሩ ያ አድራጎትም 'ከሙያቸው ጋር ግንኙነት የለውም' ሲሉ ይከራከራሉ፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG