በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታሠሩትም “በግፍ” ነበር - ተቃዋሚዎች


ተሃድሶ ወስደው ተለቀዋል የተባሉ ዜጎች - ታኅሣስ 12-2009 ዓ.ም /ፎቶ ከቴሌቪዥን ስክሪን የተወሰደ/
ተሃድሶ ወስደው ተለቀዋል የተባሉ ዜጎች - ታኅሣስ 12-2009 ዓ.ም /ፎቶ ከቴሌቪዥን ስክሪን የተወሰደ/

“ሁከት ውስጥ ተሣትፈዋል” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አሥሯቸው የነበሩ ሰዎች ትናንት በመለቀቃቸው ደስተኞች መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀድሞም መታሠራቸው አግባብ እንዳልነበረ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ያደረጉት ንግግርም ከቃላት ያለፈ የተግባር እርምጃ የሚወሰድበት ይሆናል ብለው እንደማያምኑም የፓርቲዎቹ መሪዎች ተናግረዋል፡፡

ኢሕአዴግ በጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ ማለፍ እንዳለበትና ስህተቶች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘረዘሯቸውን ችግሮች አስወግዶ መፍትኄ ለመስጠት እንደሚሠራም የገዥው ፓርቲና የመንግሥቱ መሪ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ትናንት ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፤ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ለመንግሥቱ እርምጃ የሰጧቸውን ምላሾች የያዘውን ዘገባና ከፓርቲዎቹ መሪዎች ጋር የተደረጉ የተናጠል ቃለ-ምልልሶችን ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

የታሠሩትም “በግፍ” ነበር - ተቃዋሚዎች /ዘገባ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:06 0:00

XS
SM
MD
LG