በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብር ምንዛሪ አቅም እንደማይወርድ ሚኒስትሩ ገለፁ


የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር ኢዮብ ተካልኝ
የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር ኢዮብ ተካልኝ

ኢትዮጵያ የብር ምንዛሪ አቅምን ዝቅ ልታደርግ እንደሆነ የሚሰማው “መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ የሃገሪቱ የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር ኢዮብ ተካልኝ ማስተባበላቸውን ሮይተርስ ከጆሃንስበርግ ዘግቧል።

ከለንደን የአክስዮን ገበያ ንግዶች አንዱ የሆነው ሬፊኒቲብ ኤይከን መረጃ መሠረት ዛሬ የአንድ ዶላር ኦፊሴል ምንዛሪ 53 ብር ከ42 ሣንቲም ሲሆን በጥቁር ገበያ ላይ ግን እስከ 96/97 ብር መደርሱን የዜና አውታሩ ጠቁሟል።

መንግሥቷ በአፍሪካ ኅብረት የተደገፈውን የጆሃንስበርግ የሰላም ስምምነት ከፈረመ ወዲህ ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ብድር እንዲለቀቅላት እንደምትጠብቅና ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዳለባትም እየተነገረ ነው።

ትርጉም ያለውና ጉልህ የፋይናንስ ለውጥ ማድረግ የሃገራቸው የዘወትር አጀንዳ መሆኑን ምክትል ሚኒስትር ኢዮብ ተካልኝ በሰጡት ቃል አስታውሰው ይህ ግን የምንዛሪ ግሽበት ሥጋትን የሚቀሰቅስ ሊሆን እንደማይገባው አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG