በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የዩናይትድ ስቴትስ ሥጋት

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ(ግራ) እና የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ጆኒ ካርሰን(ቀኝ)
ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ(ግራ) እና የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ጆኒ ካርሰን(ቀኝ)

“እነዚህ እርምጃዎች ሥርዓትን ለመመለስ የታሰቡ ቢሆኑ እንኳ - ነፃ ድምፆችን ማፈንና በኢትዮጵያዊያን መብቶች ውስጥ እራስን የሚጎዳ ጣልቃ ገብነት ማድረግ ለብሦቶቹ መፍትኄ ከማግኘት ይልቅ ሁኔታዎችን የሚያባብሱ ነው የሚሆኑት፡፡”

“እነዚህ እርምጃዎች ሥርዓትን ለመመለስ የታሰቡ ቢሆኑ እንኳ - ነፃ ድምፆችን ማፈንና በኢትዮጵያዊያን መብቶች ውስጥ እራስን የሚጎዳ ጣልቃ ገብነት ማድረግ ለብሦቶቹ መፍትኄ ከማግኘት ይልቅ ሁኔታዎችን የሚያባብሱ ነው የሚሆኑት፡፡”

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የውጥረት ሁኔታ ሥጋት ያደረባት መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ከአሜሪካ ድምፅ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ አስታዋቁ፡፡

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር Jonnie Carson’ም በበኩላቸው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ተጠይቀው ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት በአገሪቱ የሚታየውን ቀውስ በእጅጉ አሳሳቢ ነው።” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ላነሷቸው የመሬት መብትና የምርጫ ሕግን ማሻሻያ የመሳሰሉ ብሶቶች መልስ ለመስጠት መንግሥት ቃል መግባቱን ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለፈው መስከረም 20, 2009ዓ.ም ለፓርላማ ያሰሙትን ንግግር መንግሥታቸው እንዳጤነው ቃል አቀባዩ አመልክተዋል፡፡

ከርቢ በማከልም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ላይ የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተለይም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎችን የመያዝ፣ ነፃ ሃሣብን መገደብ፣ ሕዝዊ ስብሰባዎችን ማገድ እና የሰዓት ዕላፊ ገደብን የመሳሰሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልግበትን ሁኔታ ግልፅ እንዲያደርግ መንግሥታቸው እንደሚፈልግ አስረድተዋል፡፡

የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ፤

የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የዩናይትድ ስቴትስ ሥጋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

XS
SM
MD
LG