በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጲያ ዕለታዊ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ መረጃ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በኢትዮጲያ ባለፈው የሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ለ8191 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተካሂዶ 521 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ተረጋግጧል

የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሰረት ዛሬ ከተመረመሩት መካከል 205ቱ የቫይረሱ ተጋላጭ ሰዎች የተገኙት አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን 78 ሰዎች ቤንሻንጉል ጉምዝ፥ 71 ትግራይ ክልል፥ 47 ደቡብ ክልል፥ 41 ኦሮሚያ፥ 19 ጋምቤላ፥ 18 አፋር ክልል፥ 17 አማራ ክልል፥ 15 ድሬደዋ፥6 ሲዳማ ክልል፥ 4 ሶማሌ ክልል የተገኙ ሲሆን ሃረሪ ክልል ከተመረመሩት ውስጥ አንድም ሰው ላይ ቫይረሱ እንዳልተገኘ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል

በዛሬው ዕለት በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምክንያት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉንም የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመለክታል

ከዛሬ ጋር አጠቃላዩ በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 996 መድረሱ ታውቁዋል

በኢትዮጲያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 1ሚሊዮን 130 ሺህ 850 ሲሆን 63 ሺህ 888 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶ 24 ሺህ 493 ሰዎች ከበሽታው እንዳገገሙ መግለጫው ያሳያል

XS
SM
MD
LG