በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ


የጤና ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ
የጤና ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ

ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወደ ግዛቷ ከገባበት ካለፈው መጋቢት አንስቶ ለአንድ ቀን ከፍተኛ የሆነ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዛሬ ይፋ አድርጋለች።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ በቫይርሱ መያዛቸው ከተገለፀው 29 ሰዎች ውስጥ 19ኙ ደግሞ የጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንደሌላቸው የጤና ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያሳያል።

የጤና ሚኒስቴር የዕለቱን ሪፖርት ይፋ ካደረገ በኋላ ደግሞ የትግራይ ክልል አራት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በተናጥል ይፋ አድርጓል።

የመናበብ ችግር ተፈጥሯል ያሉት የጤና ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ ከክልሉ ጋር እየተነጋገርን ነው ብለዋል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት ምክንያቱ እየታየ ያለው መዘናጋት መሆኑንም ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ ለአሜሪካ ድምጽ አብራርተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:36 0:00
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:17 0:00


XS
SM
MD
LG