በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ24 ተከሳሾች ላይ ከስምንት ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እሥራት ፈረደ


እስከ ዕድሜ ልክ እሥራት የተበየነባቸው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ናቸው፡፡

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

ችሎቱ እንደተሰየመ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ባዘዘው መሠረት ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ ሃሳባቸውን በጽሑፍ ማቅረባቸውን ገልጿል።

አስከትሎም እንያንዳንዱ ተከሣሽ በቀረበበት ክሥ መሠረት ጥፋተኛ ሰለተባለ ያስከትላል ያለውን ቅጣት ዘርዝሯል። እንደክሡ ማመልከቻ ቅደም ተከተል አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ፋሲል የኔዓለም የዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት ተፈርዶባቸዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ ቅጣት የተጣለባቸው አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ ሲሆኑ የሃያ አምስት ዓመት ፅኑ እሥራት ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ዘጋቢአችን መለስካቸው አምሃ ሌሎቹም ተከሳሾች የተቀጡበትን ዓመታት ዝርዝር እንዲሁም ቤተሰቦችና የፖለቲካ መሪዎች ስለፍርድ ቤቱ ውሣኔ የሰጡትን መልስ አካቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ያድምጡ።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውየሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG