በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰማያዊ መሪዎች ባህርዳር ላይ ክስ ተመሠረተባቸው


- ሰማያዊ ፓርቲ የአማራ ክልላዊ መንግሥትን የፓርቲውን መዋቅሮች ለማፈራረስ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል ወነጀለ

በተቃዋሚው ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላት ላይ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትናንት የተከፈተው ክሥ

“እጅግ አስፈሪና በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ የሚገኙት የፍትሕ አካላት በገዥው ፓርቲ ተፅዕኖ ሥር መውደቃቸውን የሚያረግጥ ነው” ሲል ፓርቲው መግለጫ አውጥቷል።

የክልሉ አቃቤ ሕግ በዘጠኝ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የመሠረተው ክሥ “ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሙከራ ወንጀል” የሚል ነው።

የአማራ ክልል መንግሥት የሰማያዊ ፓርቲን መዋቅሮን ለማፈረስ የተደራጀ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ አሳስበዋል፡፡

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የክልሉ መንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን - አሁን የሚገኙት አዲስ አበባ መሆኑን ገልፀው መረጃ አሰባስበው መግለጫ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የሰማያዊ መሪዎች ባህርዳር ላይ ክስ ተመሠረተባቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG