በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ"ሕግ ሲዳኝ" መጽሐፍ ደራሲ ጋራ የተደረገ ቆይታ


ሕግ ሲዳኝ መጽሐፍ
ሕግ ሲዳኝ መጽሐፍ

"ሕግ ሲዳኝ" በሕግ ባለሞያው ሙሉጌታ አረጋዊ በቅርቡ የተጻፈ ሐሳብ ወለድ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ በሕግ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና አኹናዊ የኢትዮጵያን የሕግ ሥርዐት አቅርቦ ለመመልከት የሚጋብዝ ነው።

 ከ"ሕግ ሲዳኝ" መጽሐፍ ደራሲ ጋራ የተደረገ ቆይታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:57 0:00

"መጽሐፉ ሁላችንም አለን የምንለውን እምነት ደግመን እንድናይ ይጋብዛል" የሚሉት ደራሲው ሙሉጌታ አረጋዊ፣ "መታሰቢያነቱም እምነታቸውን ደግመው ለመጠየው ፈቃደኛ ለኾኑ ብየዋለኹ" ብለውናል። ኢትዮጵያ ውስጥ “ልክ ነኝ” ብሎ የማመን ችግር እንዳለ መረዳታቸውን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ፣በመጽሐፉ ውስጥ የተሳሉት ገጸ ባሕሪያትም "ልክ ነኝ" የሚል መከራከሪያ ይዘው ሙግት እንደሚገጥሙ ይናገራሉ።

የሕግ ባለሞያው ሙሉጌታ አረጋዊ
የሕግ ባለሞያው ሙሉጌታ አረጋዊ

ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕግ ፣ ዳኛ በፍትሕ ሥርዐቱ ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው ባለሞያዎች ወደ እራሳቸው ተመልክተው "ትንሽ ተሳስቼ ሊኾን ይችላል" በሚል በመጠራጠር ቢያስቡ የተሸላ ሕይወት የመኖር ዕድል ይኖራል ብለው እንደሚያምኑ አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል። ይሕንን አስተሳሰባቸውን ከሕግ ፍልስፍና ጋራ በማዋሐድ በመጽሐፋቸው ውስጥ እንዲንጸባረቅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በመጽሐፉ ይዘት ዙሪያ አነጋግረናቸዋል። ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG