በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጉዳይ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ካለው ካለፈው ቅዳሜ ጥቃት በኋላ፣ በዓድማው መሪነት በተጠረጠሩት ጀነራል ዓላማና ፍላጎት ዙሪያ ጥያቄዎች ተነሱ መሆናቸው ተነገረ።

ትናንት ሰኞ እንደዘገብነው፣ ብርጌዲዬር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ሊያመልጡ ሲሉ በፖሊስ ታድነው መገደላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው ጣሰው ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። ጀነራል አሳምነው የአማራ ክልል የሰላምና የደኅንነት ቢሮ ኃላፊ እንደነበሩም ይታወቃል።

ብጋዲዬር ጀነራል አሳምነው ባለፈው ቅዳሜ፣ የአማራ ክልላዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩትን፣ አማካሪያቸውንና የክልሉን ዐቃቤ ህግ እንደገደሉ ነው በፌዴራል መንግሥቱ የተወነጀሉት።

በሌላ ነገር ግን በተያያዘ ዜና፣ የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር ሹሙ ጀነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከባሕር ዳር 500 ኪሎ ሜትር ርቀት፣ አዲስ አበባ ላይ፣ በጠባቂያቸው መገደላቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አስታውቋል።

ስለ ኢትዮጵያ እንደሚያጠናና እንደሚፅፍ የተገለፀው ጋዜጠኛ ዘካርያስ ዘላለም ከቪኢኤ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፣ ጀነራል አሳምነው ረዥምና ውብስብ ታሪክ ያላቸው ሰው መሆናቸውን ተናግሯል።

ጀነራሉ፥ በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ፣ እአአ በ2009 ዓም በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተጠርጥረው መታሰራቸን የሚናገረው አቶ ዘካርያስ፣ ከሌሎች ሃያ የሚሆኑ ወታደራዊ መኰንኖች ጋር የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸውም ነበር ብሏል።

በኋላም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር ከእስር ተፈተው፣ የተሸረ ማዕርጋቸውና ጡረታቸው ተከብሮላቸው በመንግሥቱ ውስጥ እንዲያገለግሉ ተደርገው እንደነበር፣ ጋዜጠኛ ዘካርያስ ተናግሯል።

በተጠርጣሪው ጀነራልና በመንግሥቱ መካከል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ ቅራኔ መከሰቱን ዘካርያስ ቢናገርም፣ ለቅዳሜው ያልታሰበና ድንገተኛ አደጋ ምልክት ሰጪ የሆነ አንዳችም ፍንጭ የለም። እንዴውም፣ የጥቃቱ ዓላማና ሚክናት ከቶውም አይታወቅ ብሏል፡፡

«በክልል ውስጥ የተካሄደን ጥቃት እንደምን መፈንቅለ መንግሥት ብሎ ለመፈረጅ እንደሚቻል አይገባኝም ያለው ዘካርያስ፣ «የአንድን ክልል ርዕሰ ከተማ መቆጣጠር፣ በክልሉ ያሉ የፌዴራሉን ጦር ሰፈሮች ሳይጨምር፣ ሙሉውን ክልል ለመቆጣጠር ዋስትና አይሆንም» ብሏል።

የሂውማን ራይትስ ዋች ተመራማሪ ፍሌክስ ሆርኒ ጥቃቱን ለየት ባለና ጎሣ ውስጥ ከተፈጠረ ውጥረት አንፃር ነው የተመለከተው። ከፎሬን ፖሊሲ መፅሔት ጋር ባካሄደው ቃለ ምልልስ፣ የአማራው የጎሳ ቡድን በኦሮሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በዶ/ር ዐቢይ መንግሥት ላይ እርካታ ማጣቱን ጠቁሟል።

ሆርኒ የቢርጌዲዬር ጀነራል አሳምነውን ሹመት፣ የአማራው ቡድን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ የተቸረ አድርጎ ነው የሚያየው።

በክልሉ ሥልጣን ያለው የአማራው ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ የጣምራው ገዢው ፓርቲ አካል ነው። ዳሩ ግን፣ በአንዳንድ ብሔርተኛ አማሮች ዘንድ፣ አቅመ-ቢስ ተደርጎ ነው የሚታየው።

«ጀነራል አሳምነው የአማራው ክልል የደኅንነትና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው፣ የአማራውን የብሔርተኛነት ስሜት ለማርገብ እንደሆነ፣ ብዙዎች ያምናሉ» ሲል፣ ሆርኒ ከፎረን ፖሊሲ መፅሔት ጋር ባደረው ቃለ መጠይቅ ተናግሯል።

ያ ዕቅድ ግን፣ ተቃራኒ ውጤት ነው ያስከተለው። ጀነራሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ቁጣና ንዴት ሲያሰሙ ተስተውለዋል። ጠንካራ ተቃዋሚ ንግግሮችን ሲያስሙም ተደምጠዋል።

ይህ ሁሉ ሆኖ፣ ዛሬ ማክሰኞ ድረስም ግን፣ የቢርጌዲየር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ትክክለኛ ዓላማና ግብ ግልፅ አይደለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን አስክሬን ላሊበላ አየር ማረፊያ መድረሱን፣ በስፍራው የሚገኙት የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ለቢቢሲ ገለጹ።

ትናንት የብ/ጄነራል አሳምነው መገደል ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቻቸው፣ አስክሬናቸው በክብር እንዲሰጣቸው ለወረዳው መንግሥት ጥያቄ በማቅረባቸው፣ ጥያቄያቸውን የክልሉ መንግሥት ተቀብሎ አስክሬናቸውን እንደሸኘ አቶ ማንደፍሮ ተናግረዋል።

የጄነራሉ ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የአካባቢው የመንግሥት አመራር አካላት፣ የፀጥታ ኃይሎችና የቤተክርስቲያን ቀሳውስት በአውሮፕላን ማረፊያው ተገኝተዋል።

ከቤተሰቻቸው ጋር ገና ስላልተነጋገሩ የብ/ጄነራሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት የትና መቼ እንደሚፈፀም በእርግጠኝነት መግለፅ እንደማይችሉ የገለፁልን ምክትል ከንቲባው፤ ሕብረተሰቡ ኃዘኑን የሚገልፅበት በከተማ አደባባይ ትልቅ ድንኳን የተዘጋጀ መሆኑንና አስክሬናቸውም በዚሁ ድንኳን ውስጥ እንደሚያርፍ አስረድተዋል።

በዚያው ሥፍራ ሌሊቱን የፀሎተ ፍትሃት እየተደረገ እንደሚያድር መረጃ እንዳላቸውም ገልፀውልናል።

ምክትል ከንቲባው አክለውም፣ ብ/ጄነራል አሳምነው ለአገር ያበረከቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውን በደማቅ ሁኔታ ለመፈፀም ኮሚቴ መዋቀሩን አክለዋል።

አቶ ማንደፍሮ እንደገለፁልን፣ ትናንት ብ/ጄነራሉ መገደላቸው ከተሰማ አንስቶ፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ የተዘበራራቀ ስሜት እንደሚታይ እንዲሁም፣ በክልሉ አመራሮች ሞት ምክንያት፣ ድንጋጤ ውስጥ ናቸው።

የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራርና የፀጥታ አካላት ከሕዝቡ ጎን በመሆን ቤተሰባቸውን በማፅናናትና ሕዝቡንም በማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነም፣ ኦቶ ማንደፍሮት አስረድተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG