በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጉዳይ


ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን ትናንት ቅዳሜ በጠባቂያቸው መገደላቸውን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አስታወቁ። ይህ የሆነው፣ በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መካሄዱ በባለሥልጣናት ይፋ ከተደረገ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መሆኑምን ታውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፕሬስ ክፍል ቃል አቀባይ እንደገለፁት፣ ኤታ ማዦር ሹሙ እና በጡረታ ላይ የሚገኙ አንድ ጀነራል የተገደሉት፣ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ቤት ውስጥ እንዳሉ ነው።

ቢልለኔ ሥዩም እንደተናገሩት፣ አንድ ገዳይ ቡድን አማራ ክልላዊ መስተዳድር ዋና ከተማ ውስጥ በሚካሄድና ስብሰባ በመግባት ዋና አስተዳዳሪውንና አንድ ከፍተኛ አማካሪያቸውን ገድሏል።

የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ የክልሉ የደኅንነት ጥበቃ ዋና ኃላፊ ጀነራል አሳምነው ፅጌ መሆናቸውን፣ የመንግሥት መገናኛ አውታር ዘግቧል። ጠባቂያቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን ጀነራሉ ግን አልተያዙም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG