በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሙሥና የተጠረጠሩ ክሥ ተመሠረተባቸው


ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንplease wait

No media source currently available

0:00 0:04:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ዕውቅ ነጋዴዎች ላይ ትናንት ክሥ መሥርቷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ አምስተኛ የወንጀል ችሎት ትናንትና ዛሬ በዋለው ችሎት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የነበሩት የአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፣ እንዲሁም አንዳንድ ከፍተኛ ነጋዴዎች በሃገሪቱ ላይ በመቶዎች ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት በማድረስ ተከስሰዋል።

የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሦስት የተለያዩ መዝገቦች፤ ባጠቃላይ በአርባ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ከመቶ በላይ ክሦችን መመሥረቱ ታውቋል።

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው እሥራት የተጀመረው ባለፈው ዓመት ግንቦት ጀምሮ መሆኑ አይዘነጋም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG