በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተፃራሪ ምዘናዎች በታዩበት የፕሪቶርያ ስምምነት ዓመታዊ አፈጻጸም ሙሉ ትግበራው ሰፊ ጊዜንና ገንዘብን እንደሚሻ መንግሥት ገለጸ

ተፃራሪ ምዘናዎች በታዩበት የፕሪቶርያ ስምምነት ዓመታዊ አፈጻጸም ሙሉ ትግበራው ሰፊ ጊዜንና ገንዘብን እንደሚሻ መንግሥት ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00

ተፃራሪ ምዘናዎች በታዩበት የፕሪቶርያ ስምምነት ዓመታዊ አፈጻጸም ሙሉ ትግበራው ሰፊ ጊዜንና ገንዘብን እንደሚሻ መንግሥት ገለጸ

በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም፣ በቀጣይ ከእስከ አሁኑ የላቁ ተግባራት መኖራቸውን የጠቆመው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አንድ ዓመት ባስቆጠረው የድኅረ ስምምነቱ ጊዜ ውስጥ፣ በጎ ርምጃዎች ተወስደዋል፤ አለ።

ሂዩማን ራይትስ ዎች በበኩሉ፣ የሰላም ስምምነቱን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ ግጭትን በዘላቂነት ለማቆም ከተፈረመው ስምምነት በኋላም፣ ውጊያ እና ከባድ የመብቶች ጥሰት መቀጠሉ፣ በዓመት በዓሉ ላይ ጥላ አጥልቷል፤ ብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ስለ ስምምነቱ አተገባበር ተጠይቀው፣ ለተሟላ ትግበራው ሰፊ ጊዜ እና ፋይናንስ እንደሚሻ አመልክተዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባወጡት መግለጫ ደግሞ፣ የስምምነቱን ዓመታዊ አፈጻጸም አድንቀዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት እና የዐሥር ሀገራት ኤምባሲዎችም፣ የሰላም ስምምነቱን አንደኛ ዓመት አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG