ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ጉባዔ - ኢሰመጉ ይባል የነበረውና ስሙን እንዲለውጥ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ - ሰመጉ እየተባለ የሚጠራው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ተሟጋቹ ድርጅት ዛሬ ያወጣው መግለጫ ይህ ውል በሁለቱ አካላት መካከል ቢፈረም ሕገወጥ እንደሆነ ይቆጥረዋል፡፡
የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ሞላ ለቪኦኤ እንዳስረዱት የሃገሪቱን የበላይ ሕጎች የሚጥሱ ውሎችን ማንም መዋዋል አይችልም፤ ይህ ውል በአታሚዎችና በአሣታሚዎች መካከል ቢፈረም ደግሞ የሚጣሱ ሕግጋት ከሕገመንግሥቱ ይጀምራሉ ይላሉ፡፡
ሕገ ወጥ ያለውን ይህንን የውል ሠነድ መንግሥት እንዲያግድ ጉባዔው ጥሪ አቅርቧል።
ለተጨማሪ ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ