በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ከቦዪንግ 31 ጄት ገዛች


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃያ ማክስ 737 ሞዴሎችን ጨምሮ 31 አይሮፕላኖችን ከቦዪንግ ለመግዛት ሰሞኑን ውል መግባቱን አስታውቋል።

በአፍሪካ አንጋፋውና ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃያ አንድ 737 ማክስ እና አሥራ አንድ 787 ድሪምላይነር አይሮፕላኖችን ሊገዛ ከቦይንግ ጋር መፈራረሙን ይፋ ያደረገው ዛሬ ነው።

አየር መንገዱ የዛሬ አራት ዓመት ከስምንት ወር አካባቢ፤ መጋቢት 1 / 2011 ዓ.ም. ከገጠመው የማክስ ኤይት አደጋ ወዲህ እየፈፀመ ያለው የአሁኑ የቦዪንግ ግዥ “ሲንግል አይል” በሚባሉት አርበ-ጠባብ ጄቶች ላይ ያለው መተማመን መሻሻሉን እንደሚያሳይ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ቦዪንግ በበኩሉ ከአየር መንገዱ ጋር የደረሰውን ይህን ስምምነት "የዋጋ ቅናሽ ሳይደረግ የተፈፀመ በአፍሪካ ታሪክ ከፍተኛው የቦይንግ አይሮፕላኖች ግዥ" ብሎታል።

ከቢሾፍቱው የማክስ ኤይት አደጋ ማግሥት በዓለም ዙሪያ ያሉ ማክስ 737 አይሮፕላኖች በሙሉ ከአየር ላይ ወርደው ለሁለት ዓመታት ያህል የትም እንዳይነሱና እንዳይበርሩ ተደርገው ምርመራ፣ ፍተሻዎችና ማሻሻያዎች ላይ መቆየታቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ስለ አደጋው ሲናገሩ “በትውስታችን ላይ አንዳች ጠባሳ ያኖረ” ብለውታል።

በአይሮፕላኑ ላይ የነገረውን የንድፍ ጉድለት ቦዪንግ ሙሉ በሙሉ ማረሙን ማረጋገጣቸውንና በብቃትና በጥራቱ ላይ እምነታቸው መታደሱን አቶ መስፍን መግለፃቸውን የኤፒ ዘገባ አክሎ አስፍሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG