በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማኅበራዊ ሚዲያ መቋርጥ ማነጋገሩን ቀጥሏል


የማኅበራዊ ሚዲያ አርማ
የማኅበራዊ ሚዲያ አርማ

ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ በመንግሥት ከተዘጋ አምስት ቀናት ስላስቆጠረው ማኅበራዊ ሚዲያ ጽዮን ግርማ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

በኢትዮጵያ እንደ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ዩትዩብ፣ ቫይበርና ዋትስ አፕ የመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ እንዳይሠሩ ከታገዱ ዛሬ አምስተኛ ቀን አስቆጥረዋል። ተጠቃሚዎችና አስተያየት ሰጪዎች መንግሥት ሰበብ አስባብ እየፈለገ የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋቱ ኅብረተሰቡን ከሚያፍንበት ዘዴ አንዱ ነው ይላሉ።

“ይህ ደግሞ ከዚህ ቀደምም በተለያየ መንገድ ሲጠቀምበት የቆየ እና የተለመደ ነው” ይሉታል። “አሁን በፈተና ሰበብ ሙሉ ለሙሉ መዝጋት ከጀመረ ወደፊትም በየምክንያቱ መቀጠሉ አይቀርም፤ ይሕ ድርጊቱ ደግሞ ኃይሉን ሳይሆን የሕዝብ ገንዘብ ማባካኑን ያሳያል” ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። የመንግስት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ፤ “እርምጃው ተገቢ ነው ፈተናው ሲጠናቀቅ እንከፍተዋለን” ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ “ጥቁሩ ሣምንት በኢትዮጵያ” ብለውታል።

ጽዮን ግርማ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡

የማኅበራዊ ሚዲያ መቋርጥ ማነጋገሩን ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:23 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG