በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የሚታየው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ምንነት፥ ከአጣብቂኙ መውጫ መንገዶችና ዘላቂ መፍትሔዎች


አቶ በትሩ ገብረ-እግዚብሔር(ቀኝ)ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ(ግራ)
አቶ በትሩ ገብረ-እግዚብሔር(ቀኝ)ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ(ግራ)

“ዜጎች ለመብቶቻቸው ዘብ የመቆም አማራጭ በማጣታቸው ነው ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝት ያደገው።” አቶ በትሩ ገብረ-እግዚብሔር በዳላስ ቴክሳስ የሞርጌጅ ባንክ ባለ ሞያ። “ከዚህ አጣብቂኝ ለመውጣት ሌሎች በተመሳሳይ መንገድ ያለፉ አገሮችስ ምን አደረጉ? በሚል መጠየቅ ተገቢ ነው። ዓይንህን ለአፈር የሚለው የሚገባ አቋም አይመስለኝም።” ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ በዊልያም ኤንድ ሜሪ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምሕር እና የትምህርት ክፍሉ ሊቀ-መንበር።

ከአጣብቂኙ መውጫ መንገዶችና ዘላቂ መፍትሔዎች:- የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:08 0:00
ከአጣብቂኙ መውጫ መንገዶችና ዘላቂ መፍትሔዎች:- የውይይቱን ሁለተኛና የመጨረሻ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:36 0:00


በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የተቀሰሰውን ሕዝባዊ አመጽ ምንነት፥ አቅጣጫና ሁነኛ የመፍትሔ አማራጮች ለማመላከትና አድማጮችን በንቃት ለማሳተፍ የታለመ ተከታታይ ውይይት አካል ነው።

በዚህ ሁለት ክፍሎች ባሉት ውይይት፥ በኢትዮጵያ አሁን የሚታዩት ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ጨምሮ ከአጣብቂኙ መውጫ የሚረዱ ሁነኛ አማራጮችና የዜጎችን ሚና ይመረምራል።

“ኢትዮጵያዊነት” ይሰኛል። አራት የሲቪክ ቡድኖችና ማኅበሮች የመሠረቱት ድርጅት ነው። ማኅበሩ በቅርቡ ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ፥ ለመንግስታትና ለኢትዮጵያውን በጻፈው ደብዳቤ መነሻነት ከሁለት መሥራች አባላቶቹ ጋር የተካሄደ ተከታታይ ውይይት ነው።

ተወያዮቹ ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ በዊልያም ኤንድ ሜሪ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምሕር እና የትምህርት ክፍሉ ሊቀ-መንበር እና አቶ በትሩ ገብረ-እግዚብሔር በዳላስ ቴክሳስ የሞርጌጅ ባንክ ባለ ሞያ ናቸው። ሁለቱም በኢትዮጵያ ጉዳዮች በሚያደርጓቸው የረዥም ጊዜ ተሳትፎ የሚታወቁ ናቸው።

“ከወንዙ ባሻገር የሚያደርስ መንገድ፤ አሁን ካለው ሁኔታ የሚያወጣ መፍትሄ መኖሩን ሕዝቡ እንዲያውቅ እንፈልጋለን።” ነው የሚሉት የኢትዮጵያዊነት ማኅበር ተወካዮች።

XS
SM
MD
LG