ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ባለባት ከባድ የውጭ ምንዛሪ ችግር ምክንያት ሳዑዲ ዓረብያን ለአንድ ዓመት የሚበቃ ነዳጅ ዘይት ከዓመት በኋላ በሚከፈል ዱቤ እንድትሰጣት መጠየቋን የጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገለጹ፡፡
አቶ ፍጹም ትናንት ረቡዕ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል በዶላር እጥረቱና የተሟላ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት ጅቡቲ ወደብ ላይ አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ቶን ገቢ ዕቃ ማንቀሳቀስ እንዳልተቻለ አመልክቷል።
“ነዳጅ ለማስመጣት እየተነጋገርን ነን፣ ዝርዝር አፈፃጸሙ ላይ መስራት ይኖርብናል። ያ ተግባራዊ ሲሆን የነዳጅ አቅርቦቱን ለማግኘትና የውጭ ምንዛሪያችንን ለመቆጠብ ይረዳል ማለታቸውን ሮይተርስ ጠቅሷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ