ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ውጣ ውረድ የበዛበት ነበር ሲሉ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ገለፁ፡፡
ዶ/ር ጌታቸው “ኢትዮጵያና አሜሪካ፤ ታሪክ፣ ዲፕሎማሲ፣ ትንታኔ የሚል መፅሐፍ ፅፈዋል፡፡
የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ውጥን የተቋጠረው በ26ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ቴኦዶር ሩዘቬልት ጊዜ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት ከአንድ መቶ አሥር ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት በዲፕሎማሲ፣ በንግድ፣ በትምህርት፣ በወታደራዊ መስኮች፣ መተሣሰሩንና ሲጠብቅና ሲላላ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን እንደሚፈልጉ የተናገሩት ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ በአፍሪካ ላይ የተከተሉት ፖለቲካ ግን ያሣዘናቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡