የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች፣ በኢትዮጵያ እና ራስ ገዝ በሆነችው የሶማሌ ላንድ ግዛት መካከል የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ፤ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር የቴክኒክ ውይይት ማካሄዳቸውን ቱርክ አስታወቀች። ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል በተሰጋው ጉዳይ ስታሸማግል መቆየቷ ይታወሳል።
ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከሶማሊ ላንድ የባህር ጠረፍ የተወሰነውን የባህር ሰፈር በሊዝ ለመውሰድ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟን ተከትሎ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል። ድርድሩ በምላሹ ኢትዮጵያ የሶማሌ ላንድን ነፃነት በይፋ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ያደርጋታል። ቱርክ ቀጣዩ ዙር ድርድር የፊታችን መጋቢት ወር እንደሚሆን ተናግራለች።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ እንዲሁም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዴኤታ አሊ መሐመድ ኦማር የተመራ ልዑካን ቡድን በቱርክ መዲና አንካራ የመጀመሪያ ዙር የቴክኒክ ድርድር ማካሄዳቸውን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በታኅሣሥ ወር የወጣውን መግለጫ አጣቅሶ “ሁለቱም ልዑካን ለአንካራ ስምምነት እና ሐሳብ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል” ብሏል። “ይህን ራዕይ ወደ እውነታ ለመቀየር ልዑካኑ ተጨባጭ ሥራ ጀምረዋል” በማለት መግለጫው አክሏል።
ቱርክ ግዙፍ የባህር ማዶ ጦር ሰፈርን ጨምሮ በሶማሊያ ከፍተኛ የኾነ መዋዕለ ፍሰት አላት። ምንም እንኳን እራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ከተገነጠለችው ከ30 ዓመታት በላይ ቢሆንም፣ በአፍሪካ ኅብረትም ኾነ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነፃ ሀገር መሆኗ እውቅና አላገኘም። አሁንም ድረስ ሶማሊያ ሶማሊላንድን የግዛቷ አንድ አካል አድርጋ ትወስዳለች።
ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ፣ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ጋራ ከዓለም ሁሉ ወደብ አልባዋ ሀገር ነች።
መድረክ / ፎረም