በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያና የግሪክ ግንኙነት


ኢትዮጵያና ግሪክ ግንኙነታቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ማስታወቃቸው ተገለፀ።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ - የግሪክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴሬነስ ኒኮላኦስን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው ይህን ያስታወቁት።

አንድ ክፍለ ዘመን የተሻገረ የኢትዮጵያና የግሪክ ወዳጅነት የሚደነቅ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው ።

ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ በቱሪዝምና በመዋዕለ ንዋይ ምደባ መስኮች በመሰረቱት ግንኙነት ደስተኛ መሆናቸውንም አብራርተዋል። የግሪክ የንግድ ልዑካን ቡድን በነገው ዕለት አዲስ አበባ እንደሚገባም የግሪኩ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዚሁ ወቅት አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG