ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ጎንደርና ደብረ ማርቆስ ውስጥ የተመታው አድማ ዛሬ፤ ማክሰኞም ቀጥሎ መዋሉን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አስታውቋል፡፡
የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ከሥፍራው አግኝቼዋለሁ ያሉትን መረጃ መሠረት አድርገው በሰጡት ቃል በጎንደር ከተማ አቅራቢያ የተወሰኑ አካባቢዎች መጠነኛ ግጭት እንደነበረ፤ አለፋ ላይ በአራት ወረዳው ሹማምንት ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና ሰዎቹም ከአካባቢው እንዲወጡ መደረጉን፤ እሥረኞች እንዲወጡ መደረጉን አብራርተዋል፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ በበኩላቸው ከከትናንት በስተያ ዕሁድ አንስቶ በጎንደርና በደብረ ማርቆስ አገልግሎት ሰጭዎች ሥራ ማቆማቸውንና በምሥራቅ አማራ ግን ሁኔታው ሰላማዊ መሆኑን በአጠቃላይ ክልሉ እየተረጋጋ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ደብረ ማርቆስ ላይ ግን የዘጉት የተወሰኑ አገልግሎት ሰጭዎች መሆናቸውንና እነርሱም ያልሠሩት “ደርሶባቸዋል” ባሉት ማስፈራሪያ መሆኑን፤ መንግሥት ከነጋዴዎቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑንና ለደኅንነታቸው ዋስትና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል፡፡
ለሙሉው ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡