የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቢ-767 አይሮፕላን ከ ኤ320 የሕንድ አይሮፕላን ጋር ዛሬ ክንፍ ለክንፍ ተጋጭቷል።
አጋጣሚው የተፈጠረው የኒው ዴልሂው ኢንድራ ጋንዲ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ በሀገሩ ሰዓት ዛሬ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ወይም በአዲስ አበባ ሰዓት ከማለዳው 10 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አደጋው የተከሰተው በማቆሚያ ቦታ ቁጥር 86 ላይ ቆሞ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን 196 ተሣፋሪዎችን ይዞ ወደ መንደርደሪያው ለመጠጋት በትራክተር እየተገፋ ሳለ ጎኑ ላይ በማቆሚያ ቦታ ቁጥር 87 ላይ ቆሞ ከነበረው የኤር ኢንዲያው አይሮፕላን ክንፍ ጋር በመፋተጉ፡፡
በበረራ ቁጥር ET 687 ተመዝግቦ ወደ አዲስ አበባ ለመነሳት እየተዘጋጀ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET-AMG አይሮፕላንም ሆነ የኤር ኢንዲያው አይሮፕላን ሞተሮች ገና ያልተነሱ ሰለነበሩ የከፋ ጉዳይ ሳይደርስ መቅረቱ ተነግሯል፡፡
ተሣፋሪዎቹ ሁሉ ያለጉዳት እንዲወርዱ መደረጉና በረራው መሠረዙ ታውቋል።
በደንበኞቹ ላይ ለተፈጠረው ሁኔታ ይቅርታ የጠየቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በዌብሳይቱና በማኅበራዊ መገናኛዎች ባሠራጨው መልዕክት አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ለተጨማሪ ማገናኛዎቹን ተጭነው ይከተሉ፡-
http://bit.ly/2uHoh1m
https://twitter.com/flyethiopian?ref_src=twsrc%5Egoogle%7Ctwcamp%5Eserp%7Ctwgr%5Eauthor
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ