በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ13 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ፈቀደ


ፎቶ ፋይል፦ በቦረና ዞን ኬንያ ጠረፍ በሚዬ አካባቢ አርብቶ አደር ሲላላ በድርቅ ምክንያት የቀንድ ከብቶቿ ሞተውባታል፣ ውሃ ፍለጋ ረዘም ላለ ጊዜ በእግሯ ትጓዛለች፡፡
ፎቶ ፋይል፦ በቦረና ዞን ኬንያ ጠረፍ በሚዬ አካባቢ አርብቶ አደር ሲላላ በድርቅ ምክንያት የቀንድ ከብቶቿ ሞተውባታል፣ ውሃ ፍለጋ ረዘም ላለ ጊዜ በእግሯ ትጓዛለች፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለተሻሻለ የኑሮ መርኃ ግብር የዘላቂ የቦረና የውሃ ልማት ፕሮጀክት የሚውል የ13.5 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሰጥ መወሰኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ባንኩ በመግለጫው በቦረና ዘላቂ የውሃ ልማት መርኃ ግብር የአየር ንብረት ቀውሱን የሚቋቋም፣ ሥርአተ ጾታን ከግምት ያስገባና ዘላቂ የመጠጥ ውሃ እና የንጽህና አገልግሎት ተደራሽነትን ያሻሻል ብሏል፡፡

ለአራት ዓመቶ ይቆያል የተባለው የመጀመሪያው ዙር መርኃ ግብር ደረቅ በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩት ለአርብቶ አደሮቹ የማህበረሰብ አባላት፣ የመስክ መሰረተ ልማትን፣ የውሃ ማስተላለፊያ ቧንባዎች፣ እንዲሁም ህይወትን፣ ጤናን እና የምግብ ደህንነትን የሚያሻሻል እንደሚሆንም መግለጫው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG