WASHINGTON DC —
በየመቱ ከአፍሪካ አህጉር ተመርጠው የሚመጡ ወጣት መሪዎችን በሚያሰባስበውና Mandela Washington Fellowship በተባለው መርሃ ግብር በዘንድሮው ከተካፈሉት መካከል አንዱዋ ማጂ ሓይለማሪያም ትባላለች። የሃያ ስምንት አመትዋ ወጣት በአሁኑ ጊዜ በሓዋሳ ዩኒቨርስቲ የአእምሮ ጤና መምህር ስትሆን በአእምሮ ጤና እና በማህበራዊ ጥናቶች ዘርፍ ዶክትሬት ዲግሪዋን ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱዋን በመከታተል ላይ ትገኛለች።
ማጂ በሙያዋ ወደፊት አምስት የምስራቅ አፍሪካ ሃገሮችን ያካተተ የአእምሮ ጤና ምርምርና ጤና ትብብር እንዲመሰረት ጥረት ማድረግ መሆኑን ትናገራለች።
ስለቆይታዋ ለቪኦኤ ከሰጠችው ሰፋ ያለ መጠይቅ የመጀመሪያውን ክፍል ያድምጡ ።
ሙሉውን ውይይትም በእሁድ መስታወት ፕሮግራም እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።