በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተናገሩ! ራሳችሁን ወደ መድረኩ አውጡ!


ተናገሩ! ራሳችሁን ወደመድረኩ አውጡ!
ተናገሩ! ራሳችሁን ወደመድረኩ አውጡ!

ከአሜሪካ ማህበረሰብ ራስን መግለጽ ጥቅሙ ምን ያህል እንደሆነ እንማር! ምናልባት ለአይናፋር ሰዎች ስለራስ መናገር ይከብድ ይሆናል። የስነልቦና ተመራማሪዋ ሱሳን ኬይን ስለራስዋ ገልፃ መናገር ባትችልም ለመሰሎቿ ራሳቸውን በሰዎች ፊት መግለፅ ለማይችሉት፤ ተሟጋች ሆና ቀርባለች።

ሱሳን ኬይን እ.አ.አ 2012 ባሳተመችው መናገር ስኬት እንደሆነ በግልፅ አስቀምጣለች። ኬይን በመፅሃፏ አዳጊ ወጣቶችን አላማ በማድረግ ከዝምታ ይላቀቁ ዘንድ መፍትሄ ያለችውን በማስተማር ላይ ትገኛለች። የCain መፅሃፍ አላማ ወላጆችና አስተማሪዎች ራስን መግለፅ ሚስጥራዊ ሃይል እንደሆነ እንዲገነዘቡና አዳጊ ወጣቶቹን በተሻለ ራሳቸውን ሰዎች ፊት ራሳቸውን ማስተዋወቅ እንዲችሉ የሚረዳ ነው።

”ራሳቸውን መግለፅ የማይችሉ ልጆች አይናፋር ናቸው ማለት አንችልም። አንደውም የማህበረሰቡን በጎ ጎንም ሆነ ደካማ ጎን መመልከት የሚችሉ ንቁ ሰዎች ናቸው። ነገር ግን በአብዛኛው ለብቻቸው መሆን የሚያስደስታቸው፣ ፀጥ ያለ ስራን የሚመርጡ ወይንም ከአንድ ጓደኛ ጋር ብቻ መሆን የሚመቻቸው ናቸው።” ሱሳን ኬይን እንደምትለው።

ባገራችን ‘ካለመናገር ደጀአዝማችነት ይቀራል’ እንደሚባለው ፤በሰዎች ፊት ራሳቸውን ከመጠን በላይ መግለፅ የሚችሉትን ከማይችሉት ጋር በማወዳደር የሚችሉት በሕይወታቸው የተሳካላቸው ናቸው ብሎ ለመደምደም ይከብዳል።

“በዙሪያህ ያሉትን ስትመለከት ስለራሳቸው የማያወሩ ነገር ግን በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚያደርጉ ናቸው። እንደምሳሌ ብንወስድ ከአለማችን ቁንጮ ሃብታሞች መካከል ቢል ጌትስ (Bill Gates)፣ የታዋቂው የሃሪ ፖተር (Harry Potter) ፊልም እና መፅሃፍ ደራሲ ብሪቴናዊው ጄ.ኬ ሮውሊንግ (J.K. Rowling) ፣ እንዲሁም አሜሪካዊው የህፃናት መፅሃፍ ደራሲ ዶ/ር ሰዩስ (Seuss) ለአለማችን ትልቅ ሚናን እየተጫወቱ ካሉ ሰዎች መካከል ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው። ስለራሳቸው ብዙ መናገር የማይችሉ ነገርግን በየሙያቸው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የደረሱ ግለሰቦች በርካታ ናቸው።” በማለት ኬይን የህይወት ስኬት በራስ መግለጽ ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዳልሆነ አረጋግጣለች።

ራስን መግለፅ አለመቻል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ኬይን በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳጊ ወጣቶችን፣ ወላጆችንና አስተማሪዎችን አነጋግራለች። የተረዳችው ነገር ቢኖር ራስን ያለመግለፅ የብቃት ማነስ መገለጫ አንዳልሆነ ነው። በተለይም በአስተዳደራዊ ስራ ላይ እኒህ ሰዎች ሲሰማሩ ስኬታማ አንደሆኑ ልታረጋግጥ ችላለች።

ኬይን በመፅሃፏ ለወላጆችና ለአስተማሪዎች ግልፅ ይሆንላቸው ዘንድ ራስን አለመግለፅና ከሰዎች ጋር ብዙ የመግባባትን ብቃታቸው፣ ከደጅ ይልቅ ቤት ለመሆን ፍላጎት እንዳላቸውና በአጠቃላይ ስሜታቸው እንዳይጎዳ እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባ ለመግለፅ ሞክራለች። ለብቻቸው መሆን በሚፈልጉበት ሰአት ጊዜ መስጠት እንደሚያስፈልግም አበክራ ተናግራለች። ባልደረባችን ፋይዛ ኤልማስሪ (Faiza Elmasry) የዘገበችውን መስታወት አራጋው ተርጉማ ታቀርበዋለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።

ተናገሩ! ራሳችሁን ወደመድረኩ አውጡ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG