ዋሽንግተን ዲሲ —
በሐዋሳ ከተማ የተገነባው የኢንዱስትሪ መንደር ረቡእለት ተመርቆ ተከፍቷል።
ከ250 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር እንደወጣበት የተገለጸው የሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ በአጠቃላይ እስከ 60 ሺህ የሚጠጉ ስራዎችን እንደሚፈጥር ተገልጿል።
አጋሮቹም የዩናይትድ ስቴይትስ ኩባንያዎች መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድዔታ አቶ ታደሰ ሃይሌ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከበታች የሚገኘውን የድምፅ ምልክት በመጫን ከቃለ-ምልልሱ ያድምጡ።