በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሠራተኞቹን በሙሉ “በአስቸኳይ” ከኢትዮጵያ እንደሚያሰወጣ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ ከተማ

የአፍሪካ ልማት ባንክ፤ ዓለም አቀፍ ሠራተኞቹን በሙሉ “በአስቸኳይ” ከኢትዮጵያ እንደሚያሰወጣ አስታውቋል። ባንኩ ውሳኔው ላይ የደረሰው፣ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች በሠራተኞቹ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ነው።

ባለፈው ጥቅምት፣ ሁለት ሠራተኞቹ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ለሰዓታት መታገታቸውን ተከትሎ፣ ለመንግስት ችግሩን በይፋ ማሳወቁን ያመለከተው ባንኩ፣ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። “አሳሳቢ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ክስተት” ሲል ሁኔታውን ገልጾታል ባንኩ።

ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ባለሥልታናት ጋር እንዲነጋገሩ ባንኩ ከፍተኛ ልዑካኑን ወደ አዲስ አበባ ልኮ እንደነበር የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ፣ ጉዳዩ እልባት እንዳላገኘ አመልክቷል። በተጨማሪም፤ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃንም ሆነ የተደረገ ምርመራን በተመለከተ ለባንኩ ያጋራው ነገር እንደሌለም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG