በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አበበ ቢቂላ ዛሬ ተወለደ

አበበ ቢቂላ ከኦሊምፒክ አደባባይ የወርቅ ሜዳልያ የተጎናፀፈ የመጀመሪያው የጥቁር አፍሪካ ልጅ ነው። በማራቶን ሩጫ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም የአርአያነት መሠረት የጣለባቸውን ድሎቹን በ1953 ዓ.ም. ሮም ላይ በባዶ እግሩ፣ ከአራት ዓመታት በኋላ በ1957 ዓ.ም ቶኪዮ ላይ የወርቅ ሜዳልይዎችን አሸንፏል። አበበ ቶኪዮ ላይ 42 ኪሎ ሜትሩን ለመጨረስ የወሰደበት ጊዜ 2 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በማራቶን የግሉ ፈጣን ጊዜ ነው።

የረዥም ርቀት ሩጫም ባለሙያ የነበረው አበበ ቢቂላ በ1954 ዓ.ም በርሊን ላይ አሥር ሺህ ሜትር በ29 ደቂቃ ከስምንት ሰከንድ ሮጧል። አበበ ቢቂላ ጥቅምት 15/በ1966 ዓ.ም በ41 ዓመት ዕድሜው አዲስ አበባ ላይ አረፈ። ኢትዮጵያ በድፍን ዓለም እስከዛሬም በአበበ ቢቂላ ስትታወስ ትኖራለች (ከሌሎች ታሪክና እሴቶቿ ጋር)። አበበ ቢቂላ እስከዛሬም ድረስ የብዙ ብርቅ የሆኑ የአፍሪካ፣ የእስያና የአውሮፓ አትሌቶች አነቃቂና የመነሻቸው አርአያም ነው።

ተጨማሪ ይጫኑ

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG