በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ድርድር” ሊባል አይችልም- ሁለት ምሑራን -መኢአድ ይህን አይቀበለውም


በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና 16 ተቀዋሚ ፓርቲዎች ሊጀምሩት የተወሰነው “ድርድር” የመስጠትና የመቀበል መርህን የማያሟላ በመሆኑ “ድርድር” ሊባል አይችልም ሲሉ ሁለት ምሑራን ተችተውታል።

“ድርድር” ሊባል አይችልም- ሁለት ምሑራን
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:56 0:00

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞው የፍልስፍ መምሕሩን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ መመሕሩን አቶ ሙሉጌታ አረጋዊን በድርድሩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል የቀረበውን ትችት በድርድሩ ውስጥ ተሳታፊ የሆነ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እንደማይቀበለው አስታውቋል።

ፓርቲው ካቀረባቸው አጀንዳዎች ሊቀርብ የሚችል ምን የተሻለ አጀንዳ አለ? ሲሉ የፓርቲው ጸሐፊ ይጠይቃሉ። ካቀረብናቸው 15 አጀንዳዎች ውስጥ በሀገር ደረጃ የፖለቲካ እሥረኞች ይፈቱ የሚለውና የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ አጀንዳ ብቻ ነው ውድቅ የተደረገብን ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG