በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ምንነቱ ያልተለየ ነገር ትላንት በኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ሲንቀሳቀስ መታየቱን የሚጠቁም መረጃ ደርሶኛል” -  የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

ትላንት ከምሽቱ 1 ተኩል አካባቢ በሀገሪቱ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች “ሰብሰብ ያለ እና በከፍተኛ ፍጥነት የሚንቀሳቀስ ነገር ሰማይ ላይ መታየታቱን የሚያመለክት ሪፖርት ደርሶኛል” ሲል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታወቀ።

ድርጅቱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጹሑፍ በሰማይ ላይ የታየው ነገር የጠፈር ፍርስራሽ አካል አልያም ጸሃይን ከሚዞሩት አነስተኛ አለት መሰል አካላት (ሜትሮይድ) ፍንካች ሊሆን እንደሚችሉ ግምት ያሳደረ መሆኑን ጠቁሟል። ወደ ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ወዳለ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘጉ እንደነበረም ‘ደረሰኝ’ ካለው የቪዲዮ ምስል መመልከት መቻሉን ጨምሮ ገልጿል።

የክስተቱን ምንነት በተጨባጭ ለመረዳት ሁኔታውን በቅርበት እየመረመ መኾኑን ገልጾ፣ የደረሰበትን እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG