በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሠላም ድርድሩ እና ሌሎች ጉዳዮች


የሠላም ድርድሩ እና ሌሎች ጉዳዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00

የሠላም ድርድሩ እና ሌሎች ጉዳዮች

“የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር የሠላም ድርድር ለማድረግ የተቻለውን ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል” ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት፣ በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በደቡብ አፍሪካ ከትናንት በስቲያ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የአፍሪካ ኅብረት መራሹ የሠላም ውይይት መራዘሙ ከታወቀ በኋላ ነው፡፡

ዛሬ በተካሔደው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ባሰሙት ንግግር፣ መንግሥት ለሚፈጸሙበት ትንኮሳዎች ግን እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ህወሓት በበኩሉ “ትንኮሳ የሚፈጽመው እና ጥቃቱን እያስፋፋ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው” ሲል ይከሳል፡፡

ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫም “የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ኃይሎች ከትናንት ጀምሮ በራማ፣ ዛላምበሳ እና ጾረና ግንባሮች መጠነ ሠፊ ጥቃት ከፍተዋል” ሲል ወንጅሏል፡፡

ለዚህ የህወሓት ክስ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግሥታት እንደወትሮው ሁሉ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡም፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG