በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባበሩት መንግስታት ሰባኛ ጉባኤ ንግግር


ቀደም ሲልም አባል ከነበረችበት የመንግስታት ማኅበር ድጋፍ ተነፍጓት የነበረ ቢሆንም፤ በብዙ ወገኖች ትብብር እምነት ያላጣችውና ጸጥታን በጋራ የመጠበቅ ደጋፊ የሆነችው ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት መሥራች አገሮች አንዷ በመሆኗ ክብር ይሰማናል።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ በ2018ዓ.ም. ባለ መካከለኛ ገቢ ሃገር ትሆናለች፤ የሚለውን የመንግስታቸውን ሃሳብ አረጋገጡ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከጊዜው ጋር በሚሄድ ሁኔታ እንደገና እንዲዋቀር አሳሰቡ።
አቶ ኃይለ ማሪያም አክለውም፤ በዓለም አቀፉ የሰላም ጥበቃ ሥራ ኢትዮጵያ በምታዋጣው የሰራዊት ቁጥር እና በምትሰማራባቸው አካባኪዎች ብዛት ሁለተኛዋ ግዙፍ ተሳታፊ አገር መሆናን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ይህን የተናገሩት ትላንት በዋለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ እለት ባሰሙት ንግግር ነው።
ሰሎሞን አባተ ከመንግስታቱ ድርጅት ጽ/ቤት የላከውን ዝግጅት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባበሩት መንግስታት ሰባኛ ጉባኤ ንግግር 8'54"
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG