አዲስ አበባ —
ዜጎች ሃሣባቸውን የመግለፅ መብት ሲኖራቸው ሃገሮች የበለጠ ጠንካራ ይሆናሉ ሲሉ የዩናይትድ ስቴስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ አስታወቁ፡፡
አዲስ አበባ ላይ ለተሰባሰቡ ወጣቶች ሃገራቸው አፍሪካን በተመለከተ በምትከተለው ፖሊሲ ላይ ያተኮረ ንግግር ያደረጉት ኬሪ የአህጉሪቱ ዋነኛ አቅም የሚመነጨው ዜጎች ሙሉ አስተዋፅዖ ለማድረግ ካላቸው ብቃት ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ የምጣኔ ኃብት ዕድገትና ማኅበራዊ ልማትን ሊያደናቅፉ ለሚችሉት ግጭቶች መፍትሔ ሲፈልጉ የአህጉሪቱን መሪዎች ለማገዝ የኦባማ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን ሚስተር ኬሪ በዚሁ የአዲስ አበባ የፖሊሲ ንግግራቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡