በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተገለጸ


በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

ግድያውን የፈጸሙት ከህወሃት “የጥፋት ተልዕኮ የተሰጣቸው” ያሏቸው የቤንሻንጉል ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት እንደሆኑ የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ተናግረዋል። ከንቅናቄው የተሰማ ጥቃቱን የሚያረጋግጥም ይሁን የሚያስተባብል መግለጫ እስካሁን ለማግኘት አልተቻለም።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን በበኩሉ ባወጣው መግለጫ “በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጸጥታ እና ደህንነትን ለማጠናከር ፈጣን እና የተቀናጀ ርምጃ አስፈላጊ ነው” ሲል አሳስቧል።

በመተከል ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰው ገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00


XS
SM
MD
LG