በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት የስብሰባ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ


የኢትዮጵያ መንግሥት ከመጭው ሣምንት ዠምሮ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያንን ጠርቷል፡፡

ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለአንድ የአካባቢያችን ሬዲዮ ጣቢያ በሰጠው መግለጫ መሠረት የስብሰባው ዓላማ ስለ አገሪቱ አጠቃላይ ዕድገት ለማስረዳትና ለመወያየት ነው።

ይሁንና ይህንን ስብሰባ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን እንዳሉም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ ኢትዮጵያውያን ዌብ ሣይቶችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ተገልጧል።

የዚህ ስብሰባ ዓላማ ቀደም ሲል ከተገለፀው በተጨማሪ ዘርዘር ባለ መልኩ ሲገለፅ «በ፭ ዓመቱ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድና በተዘጋጀው የዳያስፖራ ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ ላይ ለማወያየት» ተብሏል። ይህም ከዋሽንግተኑ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፅ/ቤት በበረረችውና በልዩ መልዕክተኛውና ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሣደሩ አቶ ግርማ ብሩ የተፈረመችው የግብዣ ድብዳቤ ላይ ተመልክቷል።

ለምን የጥሪ ደብዳቤ አስፈለገ? አምባሣደሩ በሬዲዮ እንደገለፁት ደውሎ ማሣወቅና መመዝገብ ብቻ አይበቃም ነበር? ወዘተረፈ።

እነዚህና ሌሎችን ጥያቄዎች ለማንሳት ፈልገን ወደ ኤምባሲው ያደረግንው የስልክ ጥሪ አልተሳካም፡፡ ፀሓፊዋን አግኝቴ «ስብሰባ ላይ ናቸው፤ ሲወጡ እነግራለሁ» ብለውኝ ነበር። ቆይቼ አምባሳደር ሙሌን አግኝቼ ነበር፣ «ጠይቄ እደውልልሃለሁ» ብለውኝ ስጠባበቅ ሰዓቴ ደርሶ ወደ ስቱዲዮ ገባሁ።

ይሁንና አምባሣደር ግርማ ብሩ ለአንድ የአካባቢው ሬዲዮ ጣቢያ ስለ ዓላማው ጠቅለል አድርገው የተናገሩትን በዚህ ዘገባዬ ላይ አክያለሁ።

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG