በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ቻይና አርባ ዓመት ሞላቸው


በኢኮኖሚ አኳያ ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዋናው ግኝኙነት ያላት ከቻይና ጋር ነው ብሎ ለመከራከር ይቻላል ሲሉ በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህር መምህር ዴቪድ ሺን አመለከቱ፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ አስተዋፅዖ እያደረገች ነው ማለት ግን "በምዕራቡ ዓለም የዴሞክራሲ ግንባታን ከምንረዳበት ትርጉም አኳያ ምንም ትርጉም የለውም" ብለዋል፡፡

ረቡዕ ዕለት የቻይና ፕሬዚደንት ሁ ጂንታዎ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረችበትን አርባኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ጋር የእንኳን ደስ ያለን ሠላምታ ተለዋውጠዋል። ሚስተር ሁ በመልዕክታቸው "ምንም እንኳን በዓለም አቀፍ ደረጃና በአገሮቹ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ፈተናዎች ለውጥ ቢደቅኑም ላለፉት 40 ዓመታት ሁለቱ አገሮች ጥልቅ የጋራ ግንኙነትና ፅኑ ወዳጅነት አፍርተዋል" ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት አርባ ዓመታት ከቻይና ጋር ባፈራው ወዳጅነትና ትብብር እንደሚደሰትና ወደ ፊትም ለሁለቱ አገሮች ህዝቦች ጥቅም ግንኙነቱን እንደሚያጠብቅ ተናግረዋል።

ቀድሞ በኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ያገለገሉና በአሁኑ ሰዓት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች መምህር ዴቪድ ሺን የኢትዮጵያና የቻይናን የኢኮኖሚ ግንኙነት እና የሁለቱ ግንኙነት በተለይ በዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ያለውን አንድምታ ገምግመዋል፡፡ ዘገባውን ያዳምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG