በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮ-ቴሌኮም እና የሠራተኞቹ ውዝግብ


የኢትዮ-ቴሌኮም መሠረታዊ ሠራተኞች ማኅበር «ኢትዮ-ቴሌኮም በሠራተኞች ላይ ህገ-ወጥ እርምጃዎችን ወስዷል» ሲል ከሠሠ።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በሚል ይታወቅ የነበረውና ከኀዳር 20 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮ-ቴሌኮም እየተባለ መጠራት የጀመረው የመንግሥት የልማት ድርጅት የሠራተኞች ማኅበር ክሡን ያቀረበው ሰኔ 27 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር፡፡

የክሥ መዝገቡ የቀረበለት በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. የክሥ መዝገቡን መርምሮ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተከሣሽ ሐምሌ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. መልሱን ይዞ እንዲቀርብ ነበር፡፡ ይሁንና በቀጠሮው ዕለት ተከሣሽ መልሱን ይዞ ለመቅረብ ጊዜው አጥሮብኛል ሲል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ለወሣኝ ቦርዱ አቤት ብሏል፡፡

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርዱም የተከሣሽን አቤቱታ ተቀብሎ ሐምሌ 14 ቀን 2003 ዓ.ም. መልሱን ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ተነስቷል፡፡

ለዝርዝሩ የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG