በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊያን በሳዑዲ ዓረቢያ እሥር ቤቶች እየተሰቃዩ መሆናቸውን አስታወቁ


ሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ ባሉ በርካታ እሥር ቤቶች ውስጥ ያለ ፍትሐዊና ያለ በቂ የፍርድ ሂደት እየማቀቅን ነን ያሉ ኢትዮጵያዊያን በየአጋጣሚው ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡

የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውም ይሁኑ በሕጋዊነት ተመዝግበው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ፍፁም ኢሰብዓዊ በሆነ አያያዝ ሥር እንዳሉ ነው የሚናገሩት፡፡

እሥረኞቹ የኢትዮጵያ ኤምባሲን ለማግኘት ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ማንም እንደማይደርስላቸው አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን እንደሚያውቅና ለአሁኑ ችግርም ሆነ ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘት እየተሠራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ሰሎሞን አባተ በጂዛን እሥር ቤት ከሚገኙት የተወሰኑትን አነጋግሯል፡፡ ወደኢትዮጵያም ደውሎ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጋር ስለጉዳዩ ተወያይቷል፡፡

ቅንብሩን ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)


XS
SM
MD
LG