በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵይውያንንና ኤርትራውያንን ለማቀራረብ የሚጥረው መድረክ ሁለቱ ሀገሮች በዳግም ጦርነት ውስጥ መግባት አይኖርባቸውም ይላል።


የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ አገር ውስጥ ለማስፋት እቅድ እንዳለ ተገለጸ

ኢትዮጵያውያንንና ኤርትራውያንን ለማቀራረብ የሚደረገው ጥረት በዚህ በ United states ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ወደ አገር ውስጥም የማስፋት እቅድ እንዳላቸው ከመድረኩ መስራቾች መካካል የሆኑት አቶ አበበ ገላጋይና አቶ ሐጎስ ተክሌ አስገንዝበዋል።

"ሁለት አገሮች ብንሆንም አንድ ህዝብ ነንና መዳማት የለብንም። በድርጅታችን መሰረት ጦርነትን አንደግፍም ከጦርነት በፊት የህዝብ ለህዝብ ውይይት መቅደም ይኖርበታል" በማለት አቶ ሐጎስ ተክሌ አስረድተዋል

"በአገር ውስጥ ድርጅት ባይኖረንም ድምጻችን እዛው ይሰማል። መቼ ነው እዚህ የምንገናኘው የሚል መልዕክት ከመቀሌ ዪኒቨረሲቲ ደርሶናል። ከአዲስ አበባም ከጎንደርም ተመሳሳይ መልእክቶች ደርሰውናል"ይላሉ አቶ አበበ ገላጋይ።

XS
SM
MD
LG