በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢሮብ እና ጉሎ መኸዳ ነዋሪዎች “ኤርትራዊነት በግድ እየተጫነብን ነው” አሉ


ኤርትራና ኢትዮጵያ
ኤርትራና ኢትዮጵያ

ዜግነታቸው በኀይል እንዲቀየሩ እየተገደዱ እንደሆነ የገለጹ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ አዋሳኝ ወረዳዎች ነዋሪዎች፣ በስጋት የተሞላ ሕይወት በመምራት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ከትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ወረዳዎች መውጣቱ ሕዝቡን ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደከተተው የሚያስረዱት ነዋሪዎች እና አስተዳዳሪዎች፣ “ኤርትራውያን እንድንሆን በኀይል እየተገደድን ነው” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ዜግነታቸው በኀይል እንዲቀየሩ እየተገደዱ እንደሆነ የገለጹ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:19 0:00

በአንጻሩ፣ በኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የወጡ ጽሑፎች፣ የኤርትራ ወታደሮች በኤርትራ ልዑላዊ መሬት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል። በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኘው የኢሮብ ብሔረሰብ ተወላጆች ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ “የመጥፋት አደጋ አንዣብቦበታል’’ ባሉት የብሔረሰቡ ህልውና ጉዳይ፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ጋራ ባለፉት ሳምንታት ተገናኝተው መወያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ገብረ ገብረመድኅን፣ የጉሎ መኸዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችንና ነዋሪዎችን አናግሮ እንዲሁም፣ የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት የሰጧቸውን መግለጫዎች፣ የአካባቢው ዕውቀት ካላቸው ተንታኞች ጋራ አገናዝቦ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG