በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውንንና ኤርትራውያንን ለማቀረረብ የሚጥረው የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት መድረክ የተሻለ ውጤት እያየ መሆኑን ገለጸ


ኢትዮጵያውንንና ኤርትራውያንን ለማቀረረብ የሚጥረው የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት መድረክ የተሻለ ውጤት እያየ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያና የኤርትራ የወዳጅነት መድረክ ኢትዮጵያውንንና ኤርትራውያንን ለማቀረረብ የሚጥር ቡድን እንደሆነ ከመስራቾቹ መካከል አቶ አበበ ገላጋይና አቶ ሐጎስ ተክሌ ገልጸውልናል።

"እአአ በ2008 አም የተመሰረተው የወዳጅነት መድረክ መሰረታዊ አላማ ተመሳሳይ ባህል ታሪክና አቀማመጥ ያለውን ህዝብ በማቀራረብ ያለፈው የጦርነት ቁስል ስለሚታደስበትና ለወደፊቱ ወዳጅነት ስለሚመሰረትበት ሁኔታ ህዝብ ለህዝብ ውይይት መጀመር ነው" በማለት አቶ አበበ ገላጋይ አስረድተዋል።

አቶ ሐጎስ ተክሌ ደግሞ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን የማቀራረቡ ጥረት የተሻለ ውጤት እያሳየ መሆኑን ሲያብራሩ " በ 2008 አም ሲጀመር በጣም አነስተኛ ነበር። የቦርድ አባላትም ጥቂቶች ነበሩ። በቀጣዩ አመት አመታዊ ስብሰባ ሲካሄድ ደግሞ የተሻለ ነበረ። በሶስተኛው ጉባኤ ግን ከተለያዩ ከተማዎች የሄዱ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG