በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ለማስወገድ ማንኛውንም መንገድ እንደምትጠቀም ገለጸች


"መንግስት (የኤርትራ) ፖሊሲ እንዲቀይር አለበለዚያም እንዲቀየር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል” መለስ ዜናዊ
"መንግስት (የኤርትራ) ፖሊሲ እንዲቀይር አለበለዚያም እንዲቀየር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል” መለስ ዜናዊ

‘የሀገር ውስጥ ተቃውሞን ትኩረት ለማስቀየር የተቀናበረ ነው’ የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ

ኢትዮጵያ በምትከተለው አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የኤርትራን መንግስት ከስልጣን ለማስወገድ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ እንደምትሰራ አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራን አስመልክቶ የወሰደው የፖሊሲ አቋም ለውጥ የኤርትራ መንግስት ከጉዳይ አልቆጠረውም።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዱ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መልስ፤ መለስ የአገር ውስጥ ተቃውሞን ትኩረት ለማስቀየር ያቀናበሩት “የማይረባ” ስልት ነው፤ ብለውታል።

የኤርትራ መንግስት «የሰሜን አፍሪካን መሰል አብዮት በኢትዮጵያ ውስጥ ለማካሄድ እየጣረ ሰለመሆኑ መረጃዎች አሉን፤» ሲሉ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ሳምንት ተናግረዋል።

«ሻዕቢያ አዲስ መፈክር አውጥቷል፤ አዲስ አበባን ባግዳድ እናደርጋለን የሚል፤» ነበር፥ ያሉት አቶ መለስ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ። «ይሄን የጥፋት ኃይል የራሳችንን ድንበር ብቻ በማጠር፤ በቂ ሥራ ለመስራት ይቻላል፤ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው። ያ የመንግስት ፖሊሲ እንዲቀየር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፤» ብለዋል አቶ መለስ።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዱ በበኩላቸው፥ እንዲህ ያለው አስተያየት በሽብር ተውጦ ከሚያወራ ወገን የሚመጣ ነው፤ ሲሉ አጣጥለውታል።

የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ ስየ አብርሃ የአቶ መለስ አስተያየት «አገሪቱን ቀፍዶ የያዘውን የማኅበራዊና የምጣኔ ሃብት ቀውስ የተመለከተ ትኩረት፤» ለማስቀየር ነው፥ ይላሉ።

ከአቶ ስዬ ጋር የተድረገውን ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ፤

XS
SM
MD
LG