ቤልጅየም ውስጥ እና በአካባቢዋ ሃገሮች ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ብራስልስ ውስጥ የተቃውሞ ሠልፍ አድርገዋል፡፡
የዚህ በአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት፣ በቤልጅየም የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ፣ በቤልጅየም ሉቅማን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድርጅት ትብብር የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ አስተባባሪዎች ጥያቄዎቻቸውን በኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ተጠሪ ማስገባታቸውን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
በሆላንድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድርጅትም ሠልፉን በማቀናበር መቀላቀሉን አስተባባሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡
በሠልፉ ላይ “አውሮፓ መለስ ዜናዊን መርዳት አቁሚ፤ በኢትዮጵያ የመሬት ቅርምት ይቁም፤ ለሃይማኖታቸው ነፃነት ድምፃቸውን የሚያሰሙትን በአሸባሪነት መፈረጅ ይቁም፤ የፖለቲካ እሥረኞች ሁሉ ይፈቱ፤ የታሠሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ የሚሉ መፈክሮች ይሰሙ ነበር፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር ቃለምልልሱን ያዳምጡ፡፡