ሩሲያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሦስት የአፍሪካ ሀገራት ጋራ በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት የሚያስችላትን መመርያ ይፋ አድርጋለች፡፡
የሀገሪቱ የገንዘብ ሚንስቴር ይፋ በአደረገው መመርያ ሀገራቱ ከሩሲያ ጋራ በሚፈጽሙት ግብይት የሚያጋጥማቸውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ እና የተሻለ የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚያግዝ አስታውቋል፡፡ ከዚህ በፊት ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ጋራ ተመሳሳይ ስምምነት መፈጸሙን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ግን እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
ፕሬዝደንት ትረምፕ በትሩዝና ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ብሪክስ የተሰኘው ማኅበር አባል ሃገራት የጋራ መገበያያ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ሲያስጠነቅቁ መቆየታቸው ይታወሳል።
መድረክ / ፎረም