በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ-ቴሌኮም ለ5 ከተሞች ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ


የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ

ኢትዮ-ቴሌኮም ትናንት በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን ከተሞች የፎር (4) ጂና ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱን በአምቦ ተገኝተው ባስጀመሩበት ወቅት አምስት ከተሞችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

ሥራ አስፈፃሚዋ አገልግሎቱን ያስጀመሩበት ምክንያት ሲያስረዱም ለደምበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮ-ቴሌኮም በምእራብ ኦሮምያ ወለጋ ዞኖች ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን በተመለከተ ግን የሰጠው ምላሽ የለም።

በዚህ ዙርያ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረትም ለአሁኑ አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

ኢትዮ-ቴሌኮም ለ5 ከተሞች ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00


XS
SM
MD
LG