በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በበርበራ ጉዳይ ሥጋት አላት


የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር
የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር

በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሠነድ ጉዳይ ዩናይትድ ስቴትስን እንደሚያሳስባት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናገሩ።

ቃል አቀባዩ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ “በስምምነቱ ምክንያት በአፍሪካ ቀንድ ድንገት ያሻቀበው ውጥረት በሌሎች አጋሮች ላይ ያሳደረውን ብርቱ ሥጋት እንጋራለን” ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች ወደ ዲፕሎማሲ ንግግር እንዲገቡ ያሳሰቡት ሚለር “ዩናይትድ ስቴትስ የምታውቀው የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ በአውሮፓ አቆጣጠር በ1960 ዓ.ም. ወሰኖቿ ውስጥ ላለ ሉዓላዊነቷና የግዛቷ ጥብቅነት ነው” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG