በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ለትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት


የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ለትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:01 0:00

የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ለትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት እንዲቀጥል ጥሪ የያዘ ደብዳቤ ዛሬ ልኳል።

ደብዳቤው የተላከው ትግራይ ውስጥ ለሚገኙ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት እንደሆነ ተገልጿል።

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የተፈረመው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖደስ የወጣው ደብዳቤ የተላከው ለሽረ እንዳስላሴ የትግራይ ሰሜን ምዕራብ ሃገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፤ ለአኵስም ማዕከላዊ ዞን ሃገረሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፤ ለዓዲግራት ምሥራቃዊ ዞን ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መርሃክርስቶስ፤ ለመቐለ ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢሳያስና ለፍራሚናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ እንደሆነ ከቤተክርስትያኒቱ መሪዎች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ደብዳቤው “ጦርነቱ አላስፈላጊና በወንድማማቾች መካከል የተካሄደ፣ የከበደ የህይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት ያደረሰ” መሆኑን አስታውሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተከሰተው ሁሉ ማዘንዋ ን ይገልፃል።

ደብዳቤው በመቀጠልም "በፖለቲካ ሴራ" ብሎ በጠራው ሁኔታ ቤተክርስትያኒቱ በጊዜው “ኀዘኗን ባለመግለጿና ድርጊቱን ባለማውገዟ ትግራይ ባሉ የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ዘንድ የተፈጠረው ቅሬታ ተገቢ ነው” ብሏል።

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መሠረት ከሆነው የትግራይ ህዝብ ጋር ፖለቲከኞች ሊነጣጥሉን አይገባም” የሚለው ይህ የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ “ያለፈውን ስህተት ትተን እንደቀድሟችን ህዝባችንና ቤተክርስቲያንናችን እናገልግል” ብሏል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የሰላም ስምምነት እንዳስደሰተው የተናገረው ቅዱስ ሲኖዶስ በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት እንዲቀጥል ጠይቋል።

ለጥሪው ከሊቃነ ጳጳሳቱ በይፋ የተሰጠ መልስ ስለመኖሩ ይህ ዘገባ ለአየር አስከበቃበት ጊዜ ድረስ አይታወቅም። ትግራይ ክልል ከሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ምላሽ ለማግኘት በስልክና በአካል ያደረግኩት ጥረት አልተሳካም።

ክልሉ ውስጥ የሚገኙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን መለየታቸውን አሳውቀው "መንበረ-ሰላማ ከሳቴብርሃን ቤተክህነት" ብለው በሰየሙትና ባቋቋሙት ቤተክህነት እንደማይደራደሩና በዚያው እንደሚቀጥሉ ከትናንት በስተያ አውጥተውት በነበረ መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወቃል።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG