በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእነአንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ ብይን ላይ ተጨማሪ ተቃውሞዎች ተሰሙ


በእነአንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ ብይን ላይ ቅሬታዎቹ እየተሰሙ ያሉት በሃገር ውስጥና ከሃገርም ውጭ ከተለያዩ አካላት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ አቶ አንዱዓለም አራጌ ላይ ትላንት የሰጠው ብይን የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች አስፈጻሚውን አካል ሊቆጣጠሩ የማይችሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ነው ሲል አንድነት ፓርቲ ተቃውሞውን አሰማ።

የተፈረደባቸው እስረኞች እንግልት ተፈጽሞባቸዋል፥ የመብት መነፈግም ደርሶባቸዋል ሲል ከሷል።

ይህን የትላንቱን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በፖለቲካ ተቃውሞ መሪው አንዱዓለም አራጌና ሌሎች 22 ሰዎች ላይ የሰጠውን ብይን ያወገዘው እዚያው በኢትዮጵያ የሚገኘው አንድነት ፓርቲ ብቻ ሳይሆን በውጭም ተወግዟል።

በተለይ ዓለምአቀፍ የጋዜጠኞች መብቶች ተከራካሪዎችና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድኖች ይጠቀሳሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትና ከኮንግረሱም የሴናተር ፓትሪክ ሊሂ ቢሮም ውሣኔውን ነቅፈዋል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)


XS
SM
MD
LG